Saturday, October 29, 2011

Breaking News!

Breaking News!
In its today's session the Synod has decided for Mahibere Kidusan total denb should be changed realizing they have already been out of the church order, corrupted, labeling true church servants for the last 20 years, has numbers of accounts which the church doesn't know its where about, ... 20 key points.

The synod has thanked Aba Sereke for his effort for the last 6 years in defending to the Church making himself dedicated and abstained from any corrupt which Mahibere Kidusan use as a means to under control numbers of priests, monks, Bishops, and the Betekihnet staff. At the end the Synod has also agreed on giving a chance to Aba Sereke to work in some less pressured area for some time as using his big capacity is highly demanded by the Synod which recognized his excellent figure.

Abune Samuel has also unveiled this reality following Abune Markos significant contribution in this particular Synod.
We should thank Aba Sereke and all the synod members for letting our beloved church set free from this gangster Mahbere Kidusan.
Egziabher yimesegen!!!!!!!!!!!!!!!!!

Monday, October 3, 2011

ማህበረ ቅዱሳን የ2004 ዓ.ም. የመስቀል በዓልን ሳያከብር አሳለፈ፡፡

ማህበረ ቅዱሳን የ2004 ዓ.ም. የመስቀል በዓልን ሳያከብር አሳለፈ፡፡ By Lisanework AZ, USA






ለኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት ቀናኢ አድርጎ ራሱን ለማቅረብ ሲሞክር የነበረው ማህበረ ቅዱሳን የ2004 ዓ.ም. የመስቀል በዓልን ሳያከብር አሳለፈ፡፡

ይህ የታወቀው በበኣሉ አጋጣሚ ፓትርያርኩን ማራራት ካልቻልን አለቀልን ብሎ በነደፈው ስልቱ በተከተለው አፈጻጸም ነው፡፡

ማህበሩ የበኣሉን ትርኢትና ፅሑፍ ብሎም ማንኛውንም ነገር ፓትርያርኩ እንዲያዩለት ብዙ ደክሞ ነበር! ልብ አላደረሰለትም እንጂ፡፡

ሌሎቹ ሰንበት ተማሪዎች በድምቀት ያከበሩትን በኣል ማህበሩ ግን "እንኳን በሰላም አደረሰዎ!" በሚለው ባነሩ የፓትርያርኩ በኣለ ሲመት አስመስሎ አሳልፎታል፡፡ አዬ ፓለቲካና ሃይማኖት ማቀላቀል!!! ተጋለጡ!!!

Thursday, September 29, 2011

የ2004 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡



የሰንበት ት/ቤት መምሪያ ኃላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን በበዓሉ ተገኝተዋል::
መላው ሕዝብም ሆነ የሰንበት ተማሪዎች ማህበረ ቅዱሳን የናፈቀውን ረብሻ ሳያሳዩት ባለፉት ሦስት ዓመታት እንዳሳዩት ፍጹም ጨዋነት በዓሉን አሳልፈዋል::


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሚከበሩት ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የ፳፻፬ ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል ትናንት መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በርዕሰ ከተማችን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡

ከቀኑ ፮ ሰዓት ላይ በዋዜማ የተጀመረው አገልግሎት ቀጥሎ የዕለቱ ተረኛ የሆነው የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ሊቃውንትና ሰንበት ተማሪዎች የበዓሉን ቀለም ቃኝተው ከወረቡ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሳያቋርጥ ይወርድ በነበረው ዝናብ መሐል በትዕግስት ቆሞ በእልልታ፣ በጭብጨባና በፉጨት ደስታውንና ፍቅሩን ይገልጥላቸው ለነበረው ኢትዮጵያዊ ምዕመናን ፣ በበዓሉ ለታደሙት ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮችና፣ የውጪ ዜጎች ባስተላለፉት መልዕክት “ይኽ መስቀል የተሰጠው ለሁላችን የሰው ዘሮች ሁሉ ነው፡፡ ያልተቀበሉ ቢኖሩም ላለመቀበላቸው ምንም ምክንያት የላቸውም፡፡ ምክንያታቸው ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔር የሰጣቸው እሺና እምቢ የማለት ነጻነት ብቻ ነው፡፡… መስቀል አክባሪዎች ከሆንን ጠብና ክርክር የለም፤ የመስቀል በዓል ተሳታፊዎች ከሆንን መለያየትና መከፋፈል የለም…” በማለት ዘወትር ጠብና ረብሻ ምሳቸው የሆኑትን የአገሪቱን ገጽታ ለማበላሸት በመማሰን ላይ የሚገኙትን ጥቂት የማህበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊ ነን ባዮች መክረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በዓሉን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር “የመስቀል በዓል ሃይማኖዊ በዓል ብቻ ሳይሆን የታሪካችን አካልና የማንነታችን ዓምድና መታወቂያ ነው” ብለዋል፡፡ አቶ ኩማ የኢትጵያ ቤተክርስቲያንን ልዩ የሚያደርጋት ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር ተቻችሎ በመኖር ያበረከተችው ከፍተኛና ቀደምትነት ያለው ተሳትፎ እንደሆነ በመግለጽም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ በአምስት ቡድን የተከፋፈሉት የሰሜን፣የደቡብ፣የምስራቅ፣የምዕራብና የመካከለኛ ክፍለ ከተማ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በየተራ ትርዒት ያቀረቡ ሲሆን በትርዒቶቹም የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ ዘርና ቀለም ሳትለይ ለሰው ዘር በሙሉ ወንጌለ መንግሥቱን ስትሰብክ የኖረች መሆኗን፣የምድራችንን አረንጓዴነት መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን፣ ቤ/ክ ለአገራችን ትምህርት መስፋፋት ያደረገችውን አስተዋጽኦ ለመግለጽ ችለዋል፡፡ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር እጅግ የላቀ መሆኑ የተረጋገጠለት የሰንበት ተማሪዎቹ ትርዒት በበዓሉ የታደሙትን እጅግ የማረከ በጭብጨባ፣ በዕልልታና በፉጨት ለማጀብ ያስገደደ ነበር፡፡

በመጨረሻ ትርዒታቸውን ያቀረቡት የደብረ ጽጌ ኡራኤል ሰንበት ተማሪዎች የጡሩንባ ድምጽ ያስደነገጣቸውና መሸበራቸውን መሸፈን ያልቻሉት የማህበረ ቅዱሳን መዘምራን ትርዒታቸውን ትተው የእግሬ አውጭኝ ሩጫቸውን ሲያያዙት ተስተውለዋል፡፡ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንዲሉ ሊያስነሱት ያሰቡት ብጥብጥ ወደነሱ የዞረባቸው የመሰላቸው የማህበሩአባላት በክብር መድረክ ላይ በተቀመጡት አባ ሰረቀብርሃን ቪዲዮ እየተቀረጹ፣ ያለፈበት ፊውዳላዊ አስተሳሰባቸውን እንዲያርሙ የሚያደርግ መለኮታዊ መልዕክት ተላልፎላቸው ብዙም ትኩረት ሳይስቡ መሰስ ብለው አልፈዋል፡፡

በአጠቃላይ በዓሉ ከዚህ ቀደሞቹ በዓላት አንጻር የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቹ ተሳትፎ ደምቆ የወጣበት፣ ይወርድ የነበረው ዝናብም ሆነ ማህበረ ቅዱሳን ሊያስፈጽም የነበረው ብጥብጥ ዕድል ሳያገኙ፣ እጅግ በጣም ባማረና በደመቀ መልኩ የተከበረ በዓል ነበር፡፡ በአጠቃላይ በበዓሉ ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግርም ያልነበረ ሲሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ የበዓሉ ታዳሚዎች የተላለፈው የኢቲቪ ቀጥታ ስርጭት በተለያዩ የአገር ውስጥና የአገር ውስጥ ቋንቋዎች ስለበዓሉ ማብራሪያ ሲሰጥ አምሽቷል፡፡

Sunday, September 25, 2011

ጠባቡ የማህበረ ቅዱሳን አስተሳሰቦች by Berhane Tsegaye

ጠባቡ የማህበረ ቅዱሳን አስተሳሰቦች by Berhane Tsegaye

ካሁን በፊት ስለማኅበረ ቅዱሳን ከውጪ ሰዎች እንጂ ከማኅበሩ ሰዎች ብዙም ሲነገር አልሰማንም፡፡ ቢነገርም የማኅበሩ ሚዲያዎች የማኅበሩን ጽድቅ እንጂ ኀጢአት ሲያወሩ አላየንም፡፡ እንደችግር የሚነሡ ቢኖሩም እንኳ መከራ ደረሰብን ከሚል ያለፈ ትክክለኛ ድካምን የሚገልጽ አስተያየት እንኳ ማንበብ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ማኅበሩ ወደ ውድቀቱ እየተፋጠነ መሆኑን የሚያሳዩ አንዳን ድ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡ በአስተያየቶቹ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን የት ላይ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው የብርሃን ጸጋዬ ጽሑፍ ደጀሰላም ፌስቡክ ላይ የወጣ ነው፤ ያንብቡት::

ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ነፍሳትን ማጥመድ ስትችል በጠባብ አመለካከቶች ምክንያት ብዙዎች እድሉን ባለመጠቀም ይጠፋሉ። በ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች እድሚያቸው ከ 18 እስከ 20 ባለው ውስጥ ወደ ዩንቨርስቲዎች ይገባሉ፤ይሄ እድሜ ደግሞ ከላይ ከላይ የሚረገጥበት ጊዜ ነው ከ ከማስተዋል ይልቅ ስሜታዊነት የሚበዛበት ሲሆን እነዚህን የ ልጅ አይምሮ ያላቸውን ተማሪዎች እንዴት treat ማድረግ እንደሚቻል የታሰበት አይመስልም በግቢ ጉባኤ አስተምሮ ውስጥ ከቤተክርስቲያንዋ አስተምህሮ ጎን ለጎን የልዩነት መንገዶችን እንደ ትልቅ አስተምህሮ በየወቅቱ በመንዛት ማህበረ ቅዱሳን ከሚያስተምረው ትምህርት ውጪ ሌላው በየአውደምህረቱ ያለው አስተምህሮ በጥርጣሬ የሚታይና የተሳሳተ እንደሆነ ስብከቱ የተሀድሶ መዝሙሩ ዘፈን እንደሆነ እየተነገራቸው ይቆዩና ብዙዎቹ break ላይ ወደ ቤተሰብ እና ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የሚያነሱት ጥያቄ ሁሉ ስለ ተማሩት ትምህርት ሳይሆን የ እከሌ መዝሙር ከ እከሌ ዘፈን ጋር ይመሳሰላል ተብለናል እከሌ ተሀድሶ መናፍቅ ነው እያሉ ጥያቄና ክርክሩን ያቀልጡታል።

ስለተማሩት ትምህርት ሲጠየቁ ብዙ ያወቁት ነገር እንደሌለ ከ መልሳቸው ያስታውቃሉ ብዙዎቹ በትምህርት እያሉ በአመት ወስጥ አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን ግቢ ጉበኤ ይሳተፉና ከዛ በህዋላ የማህበረ ቅዱሳን አባል የመሆን ስሜት ለአፍታ ይሰማቸዋል ተመርቀው ከወጡም በኋላ ስለ ቤተክርስቲያን ሲወራ ሲሰሙ አዎ ግቢ እያለን እያሉ ያወራሉ ስለ መሰረታዊ የቤተክርስቲያንዋ ትምህርት ሲጠየቁ ግን ምንም። አሁን አሁን ሳስበው ማህበሩ የሚፈልገው ይሄን ይመስለኛል።

እንደሚታወቀው ብዙው የተማረው ሀይል የማህበረ ቅዱሳንነት ስሜት ካደረበት ነገ ባለስልጣን ሆነው በተለያየ የስልጣን ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ማህበሩ የሚገጥመውን ጫና የጋሩታል ይፈርዱለታል ብላችሁ ያሰባችሁ ይመስላል ግን አይደለም እናንተ በደንብ አስተምራችሁ ነፍሱን እንዲያድን ያላደረጋችሁት ባለስልጣን ማህበሩን ያድናል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። እስቲ አስቡት ዛሬም ሀገራችን ባለባት ድህነት ላይ ስንቶች በስርቆት ሀገሪትዋን ሲመዘብሩ ይኖራሉ ብዙዎቹ ታዲያ በግቢ ጉባኤ ውስጥ ያለፍን ነን የሚሉ ናቸው ምን አለ ባሉ ባልታና በክፍፍል በማይጠቅምም ወሬ በማሪዎች ላይ ከምትነዙ አትስረቅ የምትለዋን የእግዚአብሄርን ህግ በደንብ አስተምራችሁት ቢሆን ኖሮ አገራችሁንም ህዝባችሁንም በታደጋችሁ ነበር ያፈራችሁት ፍሬ ሳይሆን ቲፎዞ ነው።

በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ በሚሰጡ አስያየቶች ላይ ስሜታዊ ያልበሰሉና የማህበርተኝነት ስሜት ብቻ የሚያንጸባርቁ ብዙ ማህበርተኞችን እያየሁ ታዘዝቤአለው ይህም የትህምህርታችው ውጤት ማነስ ነው ተማሪዎቹንም ከማህበርም በላይ አስፍተው ቤተ ክርስቲያንን እንዲያዩ አስተምሩአቸው እናንተ እራሳችሁን የቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሰድርጋችሁ በመቁጠር የፈለጋችሁትን ሰው በጣም በወረደ ወንጀል በመወንጀል ግንዛቤው የሌለውን ምእመን ማህበረ ቅዱሳን አለልን ብሎ እነዲዘናጋ አድርጋችሁታል። ፈጽሞ አንድም ቀን ላልዳኑ ሰዎች ስትጨነቁ አይቼ አላውቅም እከሌን ከዚች ቤተ ክርስቲያን ሄዶልኝ አጋፍጬው እንጂ ያልተረዳውን አውቆ ድኖ ተመልሶ የሚባል ነገር እናንተ ጋር የለም የማህበሩ ችግር የቤተ ክርስቲያን ችግር ነው ብሎ በማህበሩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡ ሁሉ ለእናንተ ተሀድሶ መናፍቅ ናቸው። ሁልጊዜም የምትደክሙት ከቤተክርስቲያን በላይ ማህበሩን ለማግዘፍ ነው ሲኖዶሱን ጨምሮ ፓትሪያሪኩን ሁሉ በእናንተ መንገድና አስተሳሰብ እንዲመሩ ትሞክራላችሁ።እስቲ በየግቢው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሄዳችሁ ሀመር እና ስምአጽድቅ ጋዜጣን በነጻ አድሉና ስንቶቹ እንደሚያነቡት ተከታተሉ ያን ጊዜ ከ አቀራረባችሁ ጀምሮ ለብዞዎች መዳን ምክንያት መሆን እንዳልቻላችሁ ትረዳላችሁ።

በአጠቃላይ በእናንተ አገልግሎት ሰዎችን በሀይማኖት እንዲፀኑ ወተወታችሁ እንጂ በሀይማኖቱ ውስጥ ስላለው እውነት ጮክ ብላችሁ አልነገራችሁትም ለዚህም ነው በሀይማኖት አየኖረ በምግባር መኖር ያልቻለው ለዚህም ነው ኮሽ ባለ ቁጥር በትንሹም በትልቁም የሚደናበረው ለዚህም ነው በዩኒቨርስቲ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ወንዶቹ በሱስ ሴቶቹ በ sugar dady ሲጠቁ ይህም በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች መገለጫ ሆኖ ሳለ እናንተም ትልቁን ስራ የምንሰራው በ ግቢ ጉባኤዎች ውስጥ ነው ብላችሁ ትኩራራላችሁ ይህንንም ክፍተት ለመድፈን ውጪ ያለውን ምእመን ጨምሮ በሀይማኖት ውስጥ ያለውንም እውነት ጮክ ብለው የሚናገሩትን አገልጋዮች በየአውደምህረቱ ታሳድዳላችሁ። አሁን ባለው የስብከትና የመዝሙር አገልግሎት ምእመኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰበሰብ ምክንያት እንደሆነ ስታውቁ እነ እከሌ ያፈሩት የጉባኤ ደንበኛ እንጂ ቆራቢ አይደለም እያላቹ በጠባብ አመለካከት የተሰበሰበውን ለመበተን ሞከራችሁ ለመሆኑ እናንተ በ 20 አመት አገልግሎት ውስጥ ስንት ሰው አቆረባችሁ? ለምንስ የተሰበሰበውን ምእመን በዛው አጽንታችሁ ቆራቢ አላደረጋችሁትም? ከቻላችሁ።

አሁን ባለው የመዝሙር አገልግሎት ላይም ብዙዎቻችሁ በጥላቻና ያለ በቂ ግንዛቤ ያልሆነ አስተያየት እየሰጣችሁ ሰውን ትከፋፍላላችሁ። ለመሆኑ ዘፈንን ትቶ መዘመር ይሻላል ወይንስ ለያሬዳዊ ዜማ እንጨነቃሉ እያሉ መዝፈን ና መደነስ አይ ያሬዳዊው ዜማ እናውቃለን እሱንም እንዘምራለን የምትሉ ካላችሁ እስቲ በየቦታው ልንሰማው የምንችለው አማራጭ ስጡን። ማህበሩ የሚያሳትመውን የህብረት ዝማሬ ከሆነ እራሳችሁም ደግማችሁ አልሰማችሁትም ። ይቆየን……………………

Thursday, September 15, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን በውጪ የሚገኙ አባላቱ 1000 ዶላር በነፍስ ወከፍ እንዲያሰባስቡ ግዴታ ጣለባቸው

(ሰንበቴ፤ መስከረም 3 2003 ዓ.ም.) ማኅበረ ቅዱሳን በውጪ የሚገኙ አባላቱ 1000 ዶላር በነፍስ ወከፍ እንዲያሰባስቡ ግዴታ ጣለባቸው::


(ሰንበቴ፤ መስከረም 3 2003 ዓ.ም.)
ማህበረ ቅዱሳን ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ አባላቱ እያንዳንዳቸው 1000 ዶላር በማሰባሰብ ቤተ ክርስቲያንንና አገርን የማወክ ተግባሩን እንዲያግዙለት ጠየቀ፡፡

ማኅበሩ የመስቀል በዓልንና የጥቅምቱን ሲኖዶስ ለመበጥበጥ የያዘውን ዕቅድ በታለመለት መልኩ እያከናወነ እንደሚገኝ የውስጥ ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን የተለያዩ ተመሳሳይ ተግባራቱን ለማከናወን የሚያስችለውን እገዛም አባላቱ በአስቸኳይ እንዲያሟሉለት አሳስቧል፡፡

ማህበሩ ከገጠመው የገንዘብ እጥረት ለማገገም የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን በገዳማትና በተለያዩ መንፈሳዊ ምክንያቶች የሚሰበስበውንም ብር ጳጳሳቱን በየመኖሪያ ክፍላቸው እየተከታተለ በገንዘብና በቁሳቁስ ለማንበርከክና ሌሎች ጥቅመኞቹንም (ወልደ ሩፋኤል ፈታሂ፣ ደስታ፣ ዘሪሁን ሙላቱ፣ ዘመድኩን በቀለ፣ …) በጠራራ ጸሐይ ውስኪ ለመጠጣት እንዲያስችላቸው በገፍ እያፈሰሰላቸው የሚገኝ መሆኑን በርካታ አባላቱ አረጋግጠዋል፡፡ የዚህ ገንዘብም ዋና ምንጮችም በአሜሪካ የሚገኙ የዋህ ምዕመናንና በመርካቶ ውስጥ ‹‹ቤተክርስቲያንን እንታደግ›› በሚል የተሰባሰበው ቡድን መሆናቸው ታውቋል፡፡

በማህበሩ ከአምስት የሚበልጡት የተከፋፈሉ ቡድኖች የየራሳቸው አጀንዳ ይዘው በመንቀሳቀስ እርስ በርሳቸው በመበላላት ላይ የሚገኙ ሲሆን ማህበሩን መተዳደሪያ ያደረጉ አንዳንድ ሰራተኞችም ቤተክርስቲያኒቱ እንጀራ (ስራ) እንዲትሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ በማያያዝም ማህበሩ በተቃዋሚዎቹ ላይ ሰብአዊ ጥቃት ለማድረስ የሚያስችሉትን እንቅስቃሴዎች የማጅራት መቺዎችን፣ ነፍሰ ገዳዮችንና በጥላ ወጊነት የጥንቆላ ስራ ችሎታ ያላቸውን አካላት በማሰማራት አፈጻጸሙን እየተከታተለ የሚገኝ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማህበረ ቅዱሳን የውስጥ ችግሮቹን በማስቀየስ ለማለፍ እንዲያስችለው የነደፈው ‹‹ተሐድሶ›› የሚለው ስልት በብዙዎች ዘንድ እየተነቃበት ስለመጣ መሪዎቹ እንዳበደ ውሻ በየቦታው ለመልከስከስ እንደተገደዱ ለማየት ተችሏል፡፡ ማንነቱም እንዳይታወቅ ሽፋን የሚሰጡት የ‹‹መንግስት ደህንነት›› ሰራተኞች ነን ባዮች ጥንቃቄ የማያደርጉ ከሆነ ራሱ መንግስትንም ወደ ከፍተኛ ቀውስ ሊከቱት እንደሚችሉ አንዳንዶች አንዳንድ ምንጮች በመጠቆም ላይ ይገኛሉ፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን በመሸጥ ወደ ካቶሊክነት ገብተው በይቅርታ የተመለሱትና ፖለቲከኞችን በማስተባበር ሞያ የተካኑት አቡን ገብርኤል ሰሞኑን አዲስ አበባ ሲገቡ የማህበሩ አባላት ባደረጉላቸው ታላቅ ድግስ ውስኪና ሻምፓኝ ሲራጩ ማምሸታቸው ታውቋል፡፡ አባላቱ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ለሚበጠብጡላቸው ጳጳሳት ምግብና መጠጡን በየክፍላቸው ሲያመላልሱ ያመሹ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

Monday, September 5, 2011

ማህበረ ቅዱሳን የመስቀል በዓልን በማስታከክ ሽብር ለመፍጠር በዝግጅት ላይ ነው፡፡

(ሰንበቴ፡ ነሐሴ 30፡ 2003 ዓ.ም.) በሰንበት ት/ቤቶች ማስተባበሪያ ስር እተዳደራለሁ የሚለው ማህበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ የሞከበረውን የ2004 ዓ ም የመስቀል በዓል ለመበጥበጥ የሚያስችለው እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው፡፡ ማህበሩ በበዓሉ ላይ የሰንበት ት/ቤቶችን ወክለው መዘሙርና ትርኢት የሚያቀርቡ የአዲስ አበባ ወጣቶችን በተለያዩ አደረጃጀቶችን ተጠቅሞ በመቀስቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን በበአሉ ላይ ጥቁር ልብ አስለብሶ ሙሾ ለማስወረድ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደስራ ገብቷል፡፡

ይህ ድርጊት የአገሪቱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን መልካም ገጽታ በማጨለም ራሱን ለማጉላት ብሎም የህዝብን ትኩረት ለማስቀየስ የፈጠረው መሆኑ ተደርሶበታል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ መሰሪው ማህበር ንቡረ እድ ኤልያስን በመዝለፍ በደጀሰላም ላይ የዘገበውን ዘገባ ከብሎጉ ላይ ማጥፋቱም ተረጋግጧል፡፡ ድርጊቱም የንቡረ እዱን ቁጣ ያባባሰ እና ይህ መደረጉ በተራ ወሬዎች ወይም በተለያዩ ቁሳዊ ጥቅሞች እንደሚደልሏቸው ሰዎች የአቅዋም ለውጥ ለማሳየት የማያስገድዳቸው መሆኑን አስረግጠው መግለጣቸውን ተከትሎ የተፈጸመ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ማህበሩ የአቡነ ጳውሎስን ሞት በማፋጠን የሚፈልጋቸውን ፑፔት ጳጳሳት በማስቀመጥ እንደልቡ ለመጋለብ የቋመጠ ሲሆን ይህን ከማድረግ ሊያደናቅፉት የሚችሉትን ሁሉ በተሐድሶነት በመፈረጅ ስልቱ ቀጥሎበታል፡፡ እስካሁን ድረስም ይህ ተሐድሶ የሚለው ጽዋ ለፓትርያርኩ፣ ለአቡነ ፋኑኤል፣ ለአቡነ መልከ ጼዴቅ (ማህበሩ የመጨረሻውን ማርሽ ቀይሮ የሞታቸውን ዜና አሳምሮ በመዘገብ ወዳጃቸው ለመምሰል ቢሞክርም በርሳቸው ላይ የሠራውን ያውቀዋል)፣ አቡነ እስጢፋኖስ፣ አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ አቡነ ያሬድ፣ አቡነ ሚካኤል (ማህበሩ የመጨረሻውን ማርሽ ቀይሮ የሞታቸውን ዜና አሳምሮ በመዘገብ ወዳጃቸው ለመምሰል ቢሞክርም በርሳቸው ላይ የሠራውን ያውቀዋል)፣ መጋቤ ብሉይ ሠይፈ ሥላሴ (ማህበሩ የመጨረሻውን ማርሽ ቀይሮ የሞታቸውን ዜና አሳምሮ በመዘገብ ወዳጃቸው ለመምሰል ቢሞክርም በርሳቸው ላይ የሠራውን ያውቀዋል)፣ ንቡረ እድ ኤልያስ፣ አባ ሰረቀ፣ … ደርሷቸዋል፡፡ ሌሎቹም የጠነከረ አቋም ይዘው ሲገኙ ወደፊት የሚቀበሉት ጽዋ ይሆናል፡፡ ምን ያለበት ምን አይችልም እንዲሉ አንዳንዶቹም ከዚህ ስም ልጠፋ ለማምለጥና ጉዳቸው እንዳይገለጥ በማህበሩ ላይ የተጣበቁ ለማስመሰል እየተጣጣሩ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል፡፡

Monday, August 29, 2011

ተሐድሶ - እንደ ማህበረ ቅዱሳን

ተሐድሶ - እንደ ማህበረ ቅዱሳን
(ሰንበቴ፣ ነሐሴ 23፡ 2003 ዓ.ም.)
በአሁኑ ወቅት ማህበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን ጀርባ ላይ በመስፈንጠር አገርን የመምራት ህልሙን ለማሳካት በጭፍን በያዘው አቅጣጫው “ተሐድሶ” የሚል ነጠላ ዜማ እንደለቀቀ ተረጋገጠ፡፡

ይህ የተረጋገጠው በማሕበሩ ሚዲያ፣ በስውርና ግልጽ አመራሮቹ፣ ከቅዱሳን በረከት ለማግኘት ሳይሆን መንግሥትን በደቦ ለማማት ያመቻቸው ዘንድ በተቋቋሙ ጽዋ ማህበራትና በጭፍን በሚራመዱ አባላቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማተራመስ በማካሄድ ላይ በሚገኙት እንቅስቃሴ ነው፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን አገላለጽ “ተሐድሶ” ማለት በተግባር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰግስገው ሃይማኖትና ሥርዓትን ለመለወጥ የሚንቀሳቀሱ አካላት ሳይሆን፡-
1.በመንፈሳዊ አገልግሎታቸውና በጸጋ እግዚአብሔር ጎልተው ለወጡ ነገር ግን የማህበሩ አባላት ወይም ደጋፊ ላልሆኑ አካላት
2.በካሴትና በመጻሕፍቶች ሽያጭ ማህበሩንና ደጋፊዎቹን ከገበያ በማስወጣት ለከፍተኛ ኪሳራ ለዳረጉ ሃይሎች
3.ማህበሩ በስውርም ሆነ በግልጽ የሚያራምደውን ሀገርንና ቤተ ክርስቲያንን የሚያወድም አካሄድ እንዲያርም በግልጽ ለሚነግሩትንና ባለማስተካከሉም አቋም ለያዙ
4.የጎ2 ወይም የሸ ስውር አመራርና የዘር አሰራው ደጋፊና ተንበርካኪ ላልሆኑ
5.ማህበሩን ለማጋለጥ የሚያስችላቸው መረጃ ላላቸው
6.በማህበሩ ላልተጠመቁና ለቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አሰራር መጠናከር ለሚቀኑ
7.እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ለሚሉ
8.በነገይቱ ቤተ ክርስቲያን አማራጭ የለውጥና የጠራ አገልግሎት ኃይል በመሆን ሊቀድሙት ለሚችሉ
9.… እንቀጥላለን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚሰጥ ስም ነው፡፡

ማህበረ ቅዱሳን ይህ አቅጣጫው በአንዳንድ አካላት፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶችና ካህናት ቢነቃበትም “አይመልሰኝ” ብሎ እየሸመጠጠ ይገኛል፡፡

ማህበሩ አሁን በያዘው አቅጣጫ “ተሐድሶ ሰዎችን ላጋልጥ ነው” በማለት በስልክ የጽሑፍ መልእክትና በኢሜል ሕዝብ ይሰበስባል፣ የተሰበሰበውንም ሕዝብ ስሜት ግለት ውስጥ ከጨመረ በኋላ ዲ. ዳንኤል እንደጻፈው “ድርጅቶችን ለማለት ፈልገን ነው” በማለት ያስቀይሳል፣ በአጋጣሚ የሚጣሉት ሲያገኝም ተመሳሳይ ድስት ውስጥ ጨምሮ ይቀቅላቸዋል፣ ወዘተ እንጂ በርግጥም ተሐድሶዎቹን በማስረጃ ደግፎ አያስረዳም የማስረዳት አቅምም የለውም፡፡ ይህ አካሄድ ማህበሩ እንደ ሃያላን አገሮች ”ሽብርተኞች“ በሚል ፈሊጥ ስም እየለጠፈ የማተራመስና የፖለቲካ ልምድ ለመቅሰም አስቦ የሚያደርገው እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁን ያበደ ውሻ ሆኖ ሁሉን በመልከፍ ላይ የሚገኘው ማህበር ከአቡነ ጳውሎስና ከነበጋሻው ጋር እንዲያስታርቋቸው እጅጋየሁን አላስገባ አላስወጣ እያሉ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ደርጊት ያስተላለፉት መመሪያ፡፡




Friday, August 26, 2011

የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም. አነጋገሩ፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም. አነጋገሩ፡፡

(ሰንበቴ፡ ነሐሴ 20 2003 ዓ.ም.)የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች በአንድ በኩል በውስጥም ሆነ በውጭ እየደረሰባቸው ከሚገኘው ከፍተኛ ኪሳራና መበጥበጥ ለማገገም በሌላ በኩል እንደ ተለመደው ለጊዜው የማድፈጥ ሂደታቸውን መቀጠላቸውን የድብቅ ልሳናቸው የሆነው ደጀሰላም በመጠቆም ላይ ይገኛል፡፡
ማኅበርተኞቹ ከተጋረጠባቸው ችግር ለማምለጥ በስውርና በቆዩ አባሎቻቸው እንዲሁም በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ተጣብቀው በገዳማት ስም ማኅበሩ ከሚሰበስበው ገንዘብ በገፍ እየፈሰሰላቸው ቤተ ክርስቲያንን ለመሸጥ በተስማሙ ቢጸ ሐሳውያን ተጠቅመው ከሞት አፋፍ ለመትረፍ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
ለዚህም ማሳያ የሚሆነን እሁድ ነሐሴ 15 ቀን 2003ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ከብጹዕ ወቅዱስ አብነ ጳውሎስ ጋር ያደረጉት ውይይት ነው፡፡ ማኅበሩ በዚህ ቀጠሮ ከፓትርያርኩ ጋር ለመገናኘት እንዲችል እንደ ድልድይ ያገለገሉት፡- የፓትርያርኩ ጠባቂ ሙሉጌታ በቀለና አገልጋይ አባ እንቆ ሲሆኑ እነርሱም የሙሰኝነት ልምዱ ባላቸው በቅርብ ጊዜ የቤተክህነቱ ሕዝብ ግኑኝነት ከተባሉት (የቤተ ክህነቱ ዋነኛ ጉቦ አቀባባይና ተቀባይ ዳዊት) በኩል በርካታ ሺ ገንዘብ ለማውጣት ፈቅዷል፡፡ ለቀጠሮው መሳካት በዘማሪነት የሚታወቁ አንዲት ሴት ያበረከቱት አስተዋጽኦም የማይናቅ ነው፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩም ሕግንና ሥርዓትንና ቀኖናን ባልተከተለ መልኩ ማኅበሩ በየሆቴሉ፣ አዳራሾችና መንደር ለመንደር እያካሄደ የሚገኘው ‹‹የተሐድሶ እወጃ›› የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና ያልተከተለ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው፣ ማኅበሩ ኦዲት እንዲደረግ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በድጋሚ የተላለፈለትን መመሪይ በአስቸኳይ እንዲያስፈጽሙ፣ ለቤተክርስቲያን የሚሰጡትን አገልግሎትም ሕግንና ሥርዓትን ተከትለው እንዲፈጽሙ፣ በግልጽ የተገኙበት ችግር ሲታወቅባቸው ከማስቀየስ እንዲቆጠቡ፣ ሰከን ብለው ራሳቸውን እንዲመለከቱ የሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ልጆች አገልግሎት እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕገ ወጥ አካሄዳቸውን ሳያውቁ የሚከተሉትን ለማጀገን ታስቦ የማኅበሩ ‹‹ዘመድ›› በሆኑ ብሎጎች የተዘገበው ዘገባ ሐሰት መሆኑንና ይህ አካሄድ ማኅበሩ ላለፉት 20 ዓመታት ሲፈጽመው የቆየ ቢሆንም አሁን ግን ሁሉም ነገር ቁልጭ ብሎ ለሁሉም መታየት መቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመጨረሸም ፓትርያርኩ “ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ ለምትሠሩት ሥራ የአባት በር የሚዘጋ አለመሆኑንና ይህ በሆነበት ሁኔታ የሚረዱንን ልጆቻችንን ሁሉ ያለ አድልዎ በማስተናገድ የየድርሻቸውን እንዲወጡ ከማድረግ አንቆጠብም፡፡ ለእኛ ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ናቸው፡፡ ባልተጨበጠ ነገር መለጣጠፍም ጉዳት እንጂ ጥቅም አይኖረውም፡፡ ያለ ነገር ካለ ሁሉንም አቅርቡ፤ ከሌለ መኖር ያለብን እኛ ብቻ ነን አትበሉ፡፡ በየጊዜው የሚሰማባችሁ አቤቱታ ይህ ነው፡፡ በመዋቅር ላስቀመጥናቸው ታዘዙ፡፡ ከሰንበት ት/ቤት መምሪያው ጋር ያላችሁን አልታዘዝ ባይነት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ደግማችሁ ገልጻችኋል፡፡ እኛ ካላዘዝናችሁ የሚያዛችሁ ማነው? …” በማለት መልዕክት አስተላልፈውላቸዋል፡፡
እንደለመዱት አጭበርብረው ማለፍ የተሳናቸው የማኅበሩ አባላትም በቅርቡ (ማኅበሩንና አጋሮቹን) አስመልክቶ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተላለፈውን መመሪያና ደብዳቤ እንደሚቀበሉና መመሪያውም ትክክል እንደሆነና እንደሚደግፉት በጨው በታጠበ ዓይናቸው አረጋግጠው ተሸኝተዋል፡፡

Wednesday, February 9, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን ለማዘግየት አሁንም እየጣረ እንደሚገኝ የቤተክህነት ምንጮች አጋለጡ

ማኅበረ ቅዱሳን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን ለማዘግየት አሁንም እየጣረ እንደሚገኝ የቤተክህነት ምንጮች አጋለጡ::


• ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያን ውክልና እንደሌለው ቅዱስ ሲኖዶሰ ባደረገው ልዩ ስብሰባ ከወሰነ አንድ አመት ከመንፈቅ ሆነ

• ማኅበሩ ውሳኔውን ለማስለወጥ ደጀ ሰላም የተባለ ድህረ ገጽ በመክፈት የቤተክርስቲያን አባቶችን እና አገልጋዮችን ስም በማጥፋት እና በማስፈራራት ላይ
ይገኛል
• የበሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ማኅበሩ ከኦርቶዶክሳዊ እምነት ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን እየፈጸመ መሆኑን መረጃዎችን በመጥቀስ አስታወቀ


ማኅበረ ቅዱሳን በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጭ የቤተክርስቲያን ልጆችን ወንጌል እንዲማሩ አስተዋጽኦ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ቢገልጽም ከጊዜ ወደ ጊዜ የተነሳበትን ዓላማ እየተወ ቤተክርስቲያንን ፤አባቶችን እና ምዕመናንን በአደባባይ በማዋረድ የቤተክርስቲያንን ሃብት እና ስልጣን በእጁ ለማስገባት እየተፍጨረጨረ ይገኛል።

ይህንኑ እኩይ ተግባር ያጤኑ ብፁዓን አባቶች መስከረም 12 ቀን 2002 ዓ፡ም ማኅበሩ ያለምንም ፈቃድ ቤተክርስቲያንን ወክሎ በሁሉም አህጉረ ሰብከት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም፤ አልያም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ መዋቅር ስር በመሆን መንፈሳዊ ስራ ቢቻ እንዲሰራ፤እስካሁን የማኅበሩ አባላት በሆኑ ግለሰቦች እና በማኅበሩ ስም ያሉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቤተክርስቲያን ሃብት እና ንብረት በትክክል እንዲያሳወቅ የተወሰነ ሲሆን በወቅቱም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ማኅበሩ ባለፉት አራት እና አምስት አመታት ቢቻ በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸመውን ጥፋት እና ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ተግባራትን በዝርዝር ለብፁዓን አባቶች አቅርቦአል::የመንግስት ባለስልጣናትም ማኅበሩ የፖለቲካ ስራን በሃይማኖት ሽፋንማካሄዱን እንዲያቆም፤ ምንም መንፈሳዊ ይዘት የሌላቸውን የህትመት ውጤቶቻቸውን ዋቢ በማድረግ በዕለቱ አስታውቀዋል።
ነገር ግን እስካሁን ውሳኔው ተግባራዊ እንዳይሆን ማኅበሩ እንቅፋት እየሆነ ይገኛል። ይልቁንም ደጀ ሰላም የተባለ ብሎግ በመክፈት ምዕመናን በቤተክርስቲያን አባቶች እና በመምህራን ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው በማድረግ በየቦታው መከፋፈል እንዲበዛ በማድረግ ላይ ይገኛል። በተለይም በቅርቡ ከቤተ ክህነት 50 ገጽ ሰነድ አገኘሁ በማለት በውሸት ያስነበበው ዜና ከቤተክህነት እውቅና ውጭ የተደረገ ከመሆኑም በላይ በደፈናው በጥላቻ በመነሳሳት አጠቃላይ በቤተክርስቲያን ውስጥ ማንም መምህር እንደሌለና ምዕመኑ መሄዱን እንዲያቆም የሚቀሰቅስ አሉባልታ አዘል ዜና አስነብቦአል። ይህም ድርጊት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ ላለማድረግ ወይም ለማዘግየት ማኅበሩ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው።ይንን ጉዳይ በተመለከተ በቅርቡ ብጹአን አባቶች ዝርዝር ሃሳብ እንደሚሰጡን ቃል ገብተዋል።

ቤተክርስቲያንን በኑፋቄ ትምህርት ለማጥቃት የተነሳሱ ግለሰቦች በየቦታው እንደሚኖሩ ይታወቃል በተለይም ለመጀመሪያ ጊዜ የተሃድሶ አመራር ሆነው የተነሱት ግለሰቦች ቀደምት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እና አመራሮች እንደነበሩ ማንም የሚያውቀው ነው። ቅዱስ ሲኖዶስም የተወሰኑትን አውግዞ ለይቶአል። አሁንም ቤተክህነቱ ፈጽሞ ዝም ያለ ሳይሆን የቤተክርስቲያንን ጠላቶች ጠንካራ በሆነው መዋቅሮቹ ስር ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ላይ ይገኛል።

ማኅበረ ቅዱሳን ከመዋቅር ውጭ ሆኖ ቢቻውን ለመስራት እና የሚያስበው ግብ ላይ ለመድረስ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት የጣሰ ከመሆኑም በላይ በህግ የሚያስጠይቀው ይሆናል። ባለፈው ወር ከመጋቢ ሐዲስ በጋሻው ደሳልኝ ጋር በድሬዳዋ ተካሶ ማኅበሩ መረታቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። አሁንም የደጀ ሰላም ረፖርትሮች እንደሆኑ በታወቁት ግለሰቦች እና በማኅበረ ቅዱሳን ላይ መንፈሳዊ ኮሌጆች እና ቤተክህነት ክስ ሊመሰረቱ እንደሚችሉ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ማኅበረ ቅዱሳን ከምስረታው ጀምሮ በረካታ አመራሮች የተፈራረቁበት ሲሆን አብዛኞቹ የቀድሞ አመራሮች እና ቀደምት አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ማኅበሩን ለቀዋል። ከምክንያቶቹም ዋናዋናዎቹ፡

• ገሚሶቹ ሃይማኖታቸውን ጥለው መናፍቅ እና ሃይማኖት የለሽ በመሆናቸው፤
• ገሚሶቹ በየጊዜው የሚለዋወጠውን የሀገሪቱን ፖለቲካ በመቀላቀል ደብዛቸው የጠፋ በመሆኑ፤
• ቀሪዎቹ ግን በማኅበሩ ውስጥ በሚነሱ የዘረኝነት፤የውስጥ ጥቅምና በስልጣን አለመግባባት የተነሳ ማኅበሩን ለቀዋል።

ማኅበሩ አሁን ካለበት ሁኔታ እንዲወጣ ስለሚደረገው ጥረት የተጠናከረ ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እንገኛለን፡



ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል፡፡

ሰንበቴ - SENBETIE