ተሐድሶ - እንደ ማህበረ ቅዱሳን
(ሰንበቴ፣ ነሐሴ 23፡ 2003 ዓ.ም.)
በአሁኑ ወቅት ማህበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን ጀርባ ላይ በመስፈንጠር አገርን የመምራት ህልሙን ለማሳካት በጭፍን በያዘው አቅጣጫው “ተሐድሶ” የሚል ነጠላ ዜማ እንደለቀቀ ተረጋገጠ፡፡
ይህ የተረጋገጠው በማሕበሩ ሚዲያ፣ በስውርና ግልጽ አመራሮቹ፣ ከቅዱሳን በረከት ለማግኘት ሳይሆን መንግሥትን በደቦ ለማማት ያመቻቸው ዘንድ በተቋቋሙ ጽዋ ማህበራትና በጭፍን በሚራመዱ አባላቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማተራመስ በማካሄድ ላይ በሚገኙት እንቅስቃሴ ነው፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን አገላለጽ “ተሐድሶ” ማለት በተግባር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰግስገው ሃይማኖትና ሥርዓትን ለመለወጥ የሚንቀሳቀሱ አካላት ሳይሆን፡-
1.በመንፈሳዊ አገልግሎታቸውና በጸጋ እግዚአብሔር ጎልተው ለወጡ ነገር ግን የማህበሩ አባላት ወይም ደጋፊ ላልሆኑ አካላት
2.በካሴትና በመጻሕፍቶች ሽያጭ ማህበሩንና ደጋፊዎቹን ከገበያ በማስወጣት ለከፍተኛ ኪሳራ ለዳረጉ ሃይሎች
3.ማህበሩ በስውርም ሆነ በግልጽ የሚያራምደውን ሀገርንና ቤተ ክርስቲያንን የሚያወድም አካሄድ እንዲያርም በግልጽ ለሚነግሩትንና ባለማስተካከሉም አቋም ለያዙ
4.የጎ2 ወይም የሸ ስውር አመራርና የዘር አሰራው ደጋፊና ተንበርካኪ ላልሆኑ
5.ማህበሩን ለማጋለጥ የሚያስችላቸው መረጃ ላላቸው
6.በማህበሩ ላልተጠመቁና ለቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አሰራር መጠናከር ለሚቀኑ
7.እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ለሚሉ
8.በነገይቱ ቤተ ክርስቲያን አማራጭ የለውጥና የጠራ አገልግሎት ኃይል በመሆን ሊቀድሙት ለሚችሉ
9.… እንቀጥላለን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚሰጥ ስም ነው፡፡
ማህበረ ቅዱሳን ይህ አቅጣጫው በአንዳንድ አካላት፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶችና ካህናት ቢነቃበትም “አይመልሰኝ” ብሎ እየሸመጠጠ ይገኛል፡፡
ማህበሩ አሁን በያዘው አቅጣጫ “ተሐድሶ ሰዎችን ላጋልጥ ነው” በማለት በስልክ የጽሑፍ መልእክትና በኢሜል ሕዝብ ይሰበስባል፣ የተሰበሰበውንም ሕዝብ ስሜት ግለት ውስጥ ከጨመረ በኋላ ዲ. ዳንኤል እንደጻፈው “ድርጅቶችን ለማለት ፈልገን ነው” በማለት ያስቀይሳል፣ በአጋጣሚ የሚጣሉት ሲያገኝም ተመሳሳይ ድስት ውስጥ ጨምሮ ይቀቅላቸዋል፣ ወዘተ እንጂ በርግጥም ተሐድሶዎቹን በማስረጃ ደግፎ አያስረዳም የማስረዳት አቅምም የለውም፡፡ ይህ አካሄድ ማህበሩ እንደ ሃያላን አገሮች ”ሽብርተኞች“ በሚል ፈሊጥ ስም እየለጠፈ የማተራመስና የፖለቲካ ልምድ ለመቅሰም አስቦ የሚያደርገው እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁን ያበደ ውሻ ሆኖ ሁሉን በመልከፍ ላይ የሚገኘው ማህበር ከአቡነ ጳውሎስና ከነበጋሻው ጋር እንዲያስታርቋቸው እጅጋየሁን አላስገባ አላስወጣ እያሉ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡
Hello sebete
ReplyDeleteThanks for the information, it mean a lot especially for us who are living abroad.
It is Good and would you please add more features on it?
ReplyDelete