Thursday, September 29, 2011

የ2004 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡



የሰንበት ት/ቤት መምሪያ ኃላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን በበዓሉ ተገኝተዋል::
መላው ሕዝብም ሆነ የሰንበት ተማሪዎች ማህበረ ቅዱሳን የናፈቀውን ረብሻ ሳያሳዩት ባለፉት ሦስት ዓመታት እንዳሳዩት ፍጹም ጨዋነት በዓሉን አሳልፈዋል::


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሚከበሩት ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የ፳፻፬ ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል ትናንት መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በርዕሰ ከተማችን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡

ከቀኑ ፮ ሰዓት ላይ በዋዜማ የተጀመረው አገልግሎት ቀጥሎ የዕለቱ ተረኛ የሆነው የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ሊቃውንትና ሰንበት ተማሪዎች የበዓሉን ቀለም ቃኝተው ከወረቡ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሳያቋርጥ ይወርድ በነበረው ዝናብ መሐል በትዕግስት ቆሞ በእልልታ፣ በጭብጨባና በፉጨት ደስታውንና ፍቅሩን ይገልጥላቸው ለነበረው ኢትዮጵያዊ ምዕመናን ፣ በበዓሉ ለታደሙት ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮችና፣ የውጪ ዜጎች ባስተላለፉት መልዕክት “ይኽ መስቀል የተሰጠው ለሁላችን የሰው ዘሮች ሁሉ ነው፡፡ ያልተቀበሉ ቢኖሩም ላለመቀበላቸው ምንም ምክንያት የላቸውም፡፡ ምክንያታቸው ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔር የሰጣቸው እሺና እምቢ የማለት ነጻነት ብቻ ነው፡፡… መስቀል አክባሪዎች ከሆንን ጠብና ክርክር የለም፤ የመስቀል በዓል ተሳታፊዎች ከሆንን መለያየትና መከፋፈል የለም…” በማለት ዘወትር ጠብና ረብሻ ምሳቸው የሆኑትን የአገሪቱን ገጽታ ለማበላሸት በመማሰን ላይ የሚገኙትን ጥቂት የማህበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊ ነን ባዮች መክረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በዓሉን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር “የመስቀል በዓል ሃይማኖዊ በዓል ብቻ ሳይሆን የታሪካችን አካልና የማንነታችን ዓምድና መታወቂያ ነው” ብለዋል፡፡ አቶ ኩማ የኢትጵያ ቤተክርስቲያንን ልዩ የሚያደርጋት ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር ተቻችሎ በመኖር ያበረከተችው ከፍተኛና ቀደምትነት ያለው ተሳትፎ እንደሆነ በመግለጽም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ በአምስት ቡድን የተከፋፈሉት የሰሜን፣የደቡብ፣የምስራቅ፣የምዕራብና የመካከለኛ ክፍለ ከተማ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በየተራ ትርዒት ያቀረቡ ሲሆን በትርዒቶቹም የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ ዘርና ቀለም ሳትለይ ለሰው ዘር በሙሉ ወንጌለ መንግሥቱን ስትሰብክ የኖረች መሆኗን፣የምድራችንን አረንጓዴነት መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን፣ ቤ/ክ ለአገራችን ትምህርት መስፋፋት ያደረገችውን አስተዋጽኦ ለመግለጽ ችለዋል፡፡ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር እጅግ የላቀ መሆኑ የተረጋገጠለት የሰንበት ተማሪዎቹ ትርዒት በበዓሉ የታደሙትን እጅግ የማረከ በጭብጨባ፣ በዕልልታና በፉጨት ለማጀብ ያስገደደ ነበር፡፡

በመጨረሻ ትርዒታቸውን ያቀረቡት የደብረ ጽጌ ኡራኤል ሰንበት ተማሪዎች የጡሩንባ ድምጽ ያስደነገጣቸውና መሸበራቸውን መሸፈን ያልቻሉት የማህበረ ቅዱሳን መዘምራን ትርዒታቸውን ትተው የእግሬ አውጭኝ ሩጫቸውን ሲያያዙት ተስተውለዋል፡፡ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንዲሉ ሊያስነሱት ያሰቡት ብጥብጥ ወደነሱ የዞረባቸው የመሰላቸው የማህበሩአባላት በክብር መድረክ ላይ በተቀመጡት አባ ሰረቀብርሃን ቪዲዮ እየተቀረጹ፣ ያለፈበት ፊውዳላዊ አስተሳሰባቸውን እንዲያርሙ የሚያደርግ መለኮታዊ መልዕክት ተላልፎላቸው ብዙም ትኩረት ሳይስቡ መሰስ ብለው አልፈዋል፡፡

በአጠቃላይ በዓሉ ከዚህ ቀደሞቹ በዓላት አንጻር የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቹ ተሳትፎ ደምቆ የወጣበት፣ ይወርድ የነበረው ዝናብም ሆነ ማህበረ ቅዱሳን ሊያስፈጽም የነበረው ብጥብጥ ዕድል ሳያገኙ፣ እጅግ በጣም ባማረና በደመቀ መልኩ የተከበረ በዓል ነበር፡፡ በአጠቃላይ በበዓሉ ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግርም ያልነበረ ሲሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ የበዓሉ ታዳሚዎች የተላለፈው የኢቲቪ ቀጥታ ስርጭት በተለያዩ የአገር ውስጥና የአገር ውስጥ ቋንቋዎች ስለበዓሉ ማብራሪያ ሲሰጥ አምሽቷል፡፡

4 comments:

  1. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete
  2. መስቀል አበባ!

    ReplyDelete
  3. ቃለ ህይወት ያሰማልን::

    ReplyDelete
  4. በኢቲቪ ቀጥታ ስርጭት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተላለፈው መልዕክት አድናቆት ሊቸረው የሚገባና ቤተክርስቲያን በዓለም ውስጥ የሚነሱ አጀንዳዮችን በቀጥተኛ መንገድ ማየት የሚያስችል መነጽር እንዳላት የጠቆመ ነበር፡፡

    ReplyDelete