ጠባቡ የማህበረ ቅዱሳን አስተሳሰቦች by Berhane Tsegaye
ካሁን በፊት ስለማኅበረ ቅዱሳን ከውጪ ሰዎች እንጂ ከማኅበሩ ሰዎች ብዙም ሲነገር አልሰማንም፡፡ ቢነገርም የማኅበሩ ሚዲያዎች የማኅበሩን ጽድቅ እንጂ ኀጢአት ሲያወሩ አላየንም፡፡ እንደችግር የሚነሡ ቢኖሩም እንኳ መከራ ደረሰብን ከሚል ያለፈ ትክክለኛ ድካምን የሚገልጽ አስተያየት እንኳ ማንበብ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ማኅበሩ ወደ ውድቀቱ እየተፋጠነ መሆኑን የሚያሳዩ አንዳን ድ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡ በአስተያየቶቹ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን የት ላይ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው የብርሃን ጸጋዬ ጽሑፍ ደጀሰላም ፌስቡክ ላይ የወጣ ነው፤ ያንብቡት::
ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ነፍሳትን ማጥመድ ስትችል በጠባብ አመለካከቶች ምክንያት ብዙዎች እድሉን ባለመጠቀም ይጠፋሉ። በ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች እድሚያቸው ከ 18 እስከ 20 ባለው ውስጥ ወደ ዩንቨርስቲዎች ይገባሉ፤ይሄ እድሜ ደግሞ ከላይ ከላይ የሚረገጥበት ጊዜ ነው ከ ከማስተዋል ይልቅ ስሜታዊነት የሚበዛበት ሲሆን እነዚህን የ ልጅ አይምሮ ያላቸውን ተማሪዎች እንዴት treat ማድረግ እንደሚቻል የታሰበት አይመስልም በግቢ ጉባኤ አስተምሮ ውስጥ ከቤተክርስቲያንዋ አስተምህሮ ጎን ለጎን የልዩነት መንገዶችን እንደ ትልቅ አስተምህሮ በየወቅቱ በመንዛት ማህበረ ቅዱሳን ከሚያስተምረው ትምህርት ውጪ ሌላው በየአውደምህረቱ ያለው አስተምህሮ በጥርጣሬ የሚታይና የተሳሳተ እንደሆነ ስብከቱ የተሀድሶ መዝሙሩ ዘፈን እንደሆነ እየተነገራቸው ይቆዩና ብዙዎቹ break ላይ ወደ ቤተሰብ እና ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የሚያነሱት ጥያቄ ሁሉ ስለ ተማሩት ትምህርት ሳይሆን የ እከሌ መዝሙር ከ እከሌ ዘፈን ጋር ይመሳሰላል ተብለናል እከሌ ተሀድሶ መናፍቅ ነው እያሉ ጥያቄና ክርክሩን ያቀልጡታል።
ስለተማሩት ትምህርት ሲጠየቁ ብዙ ያወቁት ነገር እንደሌለ ከ መልሳቸው ያስታውቃሉ ብዙዎቹ በትምህርት እያሉ በአመት ወስጥ አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን ግቢ ጉበኤ ይሳተፉና ከዛ በህዋላ የማህበረ ቅዱሳን አባል የመሆን ስሜት ለአፍታ ይሰማቸዋል ተመርቀው ከወጡም በኋላ ስለ ቤተክርስቲያን ሲወራ ሲሰሙ አዎ ግቢ እያለን እያሉ ያወራሉ ስለ መሰረታዊ የቤተክርስቲያንዋ ትምህርት ሲጠየቁ ግን ምንም። አሁን አሁን ሳስበው ማህበሩ የሚፈልገው ይሄን ይመስለኛል።
እንደሚታወቀው ብዙው የተማረው ሀይል የማህበረ ቅዱሳንነት ስሜት ካደረበት ነገ ባለስልጣን ሆነው በተለያየ የስልጣን ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ማህበሩ የሚገጥመውን ጫና የጋሩታል ይፈርዱለታል ብላችሁ ያሰባችሁ ይመስላል ግን አይደለም እናንተ በደንብ አስተምራችሁ ነፍሱን እንዲያድን ያላደረጋችሁት ባለስልጣን ማህበሩን ያድናል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። እስቲ አስቡት ዛሬም ሀገራችን ባለባት ድህነት ላይ ስንቶች በስርቆት ሀገሪትዋን ሲመዘብሩ ይኖራሉ ብዙዎቹ ታዲያ በግቢ ጉባኤ ውስጥ ያለፍን ነን የሚሉ ናቸው ምን አለ ባሉ ባልታና በክፍፍል በማይጠቅምም ወሬ በማሪዎች ላይ ከምትነዙ አትስረቅ የምትለዋን የእግዚአብሄርን ህግ በደንብ አስተምራችሁት ቢሆን ኖሮ አገራችሁንም ህዝባችሁንም በታደጋችሁ ነበር ያፈራችሁት ፍሬ ሳይሆን ቲፎዞ ነው።
በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ በሚሰጡ አስያየቶች ላይ ስሜታዊ ያልበሰሉና የማህበርተኝነት ስሜት ብቻ የሚያንጸባርቁ ብዙ ማህበርተኞችን እያየሁ ታዘዝቤአለው ይህም የትህምህርታችው ውጤት ማነስ ነው ተማሪዎቹንም ከማህበርም በላይ አስፍተው ቤተ ክርስቲያንን እንዲያዩ አስተምሩአቸው እናንተ እራሳችሁን የቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሰድርጋችሁ በመቁጠር የፈለጋችሁትን ሰው በጣም በወረደ ወንጀል በመወንጀል ግንዛቤው የሌለውን ምእመን ማህበረ ቅዱሳን አለልን ብሎ እነዲዘናጋ አድርጋችሁታል። ፈጽሞ አንድም ቀን ላልዳኑ ሰዎች ስትጨነቁ አይቼ አላውቅም እከሌን ከዚች ቤተ ክርስቲያን ሄዶልኝ አጋፍጬው እንጂ ያልተረዳውን አውቆ ድኖ ተመልሶ የሚባል ነገር እናንተ ጋር የለም የማህበሩ ችግር የቤተ ክርስቲያን ችግር ነው ብሎ በማህበሩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡ ሁሉ ለእናንተ ተሀድሶ መናፍቅ ናቸው። ሁልጊዜም የምትደክሙት ከቤተክርስቲያን በላይ ማህበሩን ለማግዘፍ ነው ሲኖዶሱን ጨምሮ ፓትሪያሪኩን ሁሉ በእናንተ መንገድና አስተሳሰብ እንዲመሩ ትሞክራላችሁ።እስቲ በየግቢው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሄዳችሁ ሀመር እና ስምአጽድቅ ጋዜጣን በነጻ አድሉና ስንቶቹ እንደሚያነቡት ተከታተሉ ያን ጊዜ ከ አቀራረባችሁ ጀምሮ ለብዞዎች መዳን ምክንያት መሆን እንዳልቻላችሁ ትረዳላችሁ።
በአጠቃላይ በእናንተ አገልግሎት ሰዎችን በሀይማኖት እንዲፀኑ ወተወታችሁ እንጂ በሀይማኖቱ ውስጥ ስላለው እውነት ጮክ ብላችሁ አልነገራችሁትም ለዚህም ነው በሀይማኖት አየኖረ በምግባር መኖር ያልቻለው ለዚህም ነው ኮሽ ባለ ቁጥር በትንሹም በትልቁም የሚደናበረው ለዚህም ነው በዩኒቨርስቲ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ወንዶቹ በሱስ ሴቶቹ በ sugar dady ሲጠቁ ይህም በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች መገለጫ ሆኖ ሳለ እናንተም ትልቁን ስራ የምንሰራው በ ግቢ ጉባኤዎች ውስጥ ነው ብላችሁ ትኩራራላችሁ ይህንንም ክፍተት ለመድፈን ውጪ ያለውን ምእመን ጨምሮ በሀይማኖት ውስጥ ያለውንም እውነት ጮክ ብለው የሚናገሩትን አገልጋዮች በየአውደምህረቱ ታሳድዳላችሁ። አሁን ባለው የስብከትና የመዝሙር አገልግሎት ምእመኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰበሰብ ምክንያት እንደሆነ ስታውቁ እነ እከሌ ያፈሩት የጉባኤ ደንበኛ እንጂ ቆራቢ አይደለም እያላቹ በጠባብ አመለካከት የተሰበሰበውን ለመበተን ሞከራችሁ ለመሆኑ እናንተ በ 20 አመት አገልግሎት ውስጥ ስንት ሰው አቆረባችሁ? ለምንስ የተሰበሰበውን ምእመን በዛው አጽንታችሁ ቆራቢ አላደረጋችሁትም? ከቻላችሁ።
አሁን ባለው የመዝሙር አገልግሎት ላይም ብዙዎቻችሁ በጥላቻና ያለ በቂ ግንዛቤ ያልሆነ አስተያየት እየሰጣችሁ ሰውን ትከፋፍላላችሁ። ለመሆኑ ዘፈንን ትቶ መዘመር ይሻላል ወይንስ ለያሬዳዊ ዜማ እንጨነቃሉ እያሉ መዝፈን ና መደነስ አይ ያሬዳዊው ዜማ እናውቃለን እሱንም እንዘምራለን የምትሉ ካላችሁ እስቲ በየቦታው ልንሰማው የምንችለው አማራጭ ስጡን። ማህበሩ የሚያሳትመውን የህብረት ዝማሬ ከሆነ እራሳችሁም ደግማችሁ አልሰማችሁትም ። ይቆየን……………………
God Bless you Birhane
ReplyDeleteለማህበሩ ልብ!
ReplyDeleteyehe mahiber min ale lib agignto wederasu temeliso binor. ahun yetesetew michu gize nebere
ReplyDelete