የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም. አነጋገሩ፡፡
(ሰንበቴ፡ ነሐሴ 20 2003 ዓ.ም.)የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች በአንድ በኩል በውስጥም ሆነ በውጭ እየደረሰባቸው ከሚገኘው ከፍተኛ ኪሳራና መበጥበጥ ለማገገም በሌላ በኩል እንደ ተለመደው ለጊዜው የማድፈጥ ሂደታቸውን መቀጠላቸውን የድብቅ ልሳናቸው የሆነው ደጀሰላም በመጠቆም ላይ ይገኛል፡፡
ማኅበርተኞቹ ከተጋረጠባቸው ችግር ለማምለጥ በስውርና በቆዩ አባሎቻቸው እንዲሁም በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ተጣብቀው በገዳማት ስም ማኅበሩ ከሚሰበስበው ገንዘብ በገፍ እየፈሰሰላቸው ቤተ ክርስቲያንን ለመሸጥ በተስማሙ ቢጸ ሐሳውያን ተጠቅመው ከሞት አፋፍ ለመትረፍ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
ለዚህም ማሳያ የሚሆነን እሁድ ነሐሴ 15 ቀን 2003ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ከብጹዕ ወቅዱስ አብነ ጳውሎስ ጋር ያደረጉት ውይይት ነው፡፡ ማኅበሩ በዚህ ቀጠሮ ከፓትርያርኩ ጋር ለመገናኘት እንዲችል እንደ ድልድይ ያገለገሉት፡- የፓትርያርኩ ጠባቂ ሙሉጌታ በቀለና አገልጋይ አባ እንቆ ሲሆኑ እነርሱም የሙሰኝነት ልምዱ ባላቸው በቅርብ ጊዜ የቤተክህነቱ ሕዝብ ግኑኝነት ከተባሉት (የቤተ ክህነቱ ዋነኛ ጉቦ አቀባባይና ተቀባይ ዳዊት) በኩል በርካታ ሺ ገንዘብ ለማውጣት ፈቅዷል፡፡ ለቀጠሮው መሳካት በዘማሪነት የሚታወቁ አንዲት ሴት ያበረከቱት አስተዋጽኦም የማይናቅ ነው፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩም ሕግንና ሥርዓትንና ቀኖናን ባልተከተለ መልኩ ማኅበሩ በየሆቴሉ፣ አዳራሾችና መንደር ለመንደር እያካሄደ የሚገኘው ‹‹የተሐድሶ እወጃ›› የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና ያልተከተለ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው፣ ማኅበሩ ኦዲት እንዲደረግ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በድጋሚ የተላለፈለትን መመሪይ በአስቸኳይ እንዲያስፈጽሙ፣ ለቤተክርስቲያን የሚሰጡትን አገልግሎትም ሕግንና ሥርዓትን ተከትለው እንዲፈጽሙ፣ በግልጽ የተገኙበት ችግር ሲታወቅባቸው ከማስቀየስ እንዲቆጠቡ፣ ሰከን ብለው ራሳቸውን እንዲመለከቱ የሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ልጆች አገልግሎት እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕገ ወጥ አካሄዳቸውን ሳያውቁ የሚከተሉትን ለማጀገን ታስቦ የማኅበሩ ‹‹ዘመድ›› በሆኑ ብሎጎች የተዘገበው ዘገባ ሐሰት መሆኑንና ይህ አካሄድ ማኅበሩ ላለፉት 20 ዓመታት ሲፈጽመው የቆየ ቢሆንም አሁን ግን ሁሉም ነገር ቁልጭ ብሎ ለሁሉም መታየት መቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመጨረሸም ፓትርያርኩ “ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ ለምትሠሩት ሥራ የአባት በር የሚዘጋ አለመሆኑንና ይህ በሆነበት ሁኔታ የሚረዱንን ልጆቻችንን ሁሉ ያለ አድልዎ በማስተናገድ የየድርሻቸውን እንዲወጡ ከማድረግ አንቆጠብም፡፡ ለእኛ ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ናቸው፡፡ ባልተጨበጠ ነገር መለጣጠፍም ጉዳት እንጂ ጥቅም አይኖረውም፡፡ ያለ ነገር ካለ ሁሉንም አቅርቡ፤ ከሌለ መኖር ያለብን እኛ ብቻ ነን አትበሉ፡፡ በየጊዜው የሚሰማባችሁ አቤቱታ ይህ ነው፡፡ በመዋቅር ላስቀመጥናቸው ታዘዙ፡፡ ከሰንበት ት/ቤት መምሪያው ጋር ያላችሁን አልታዘዝ ባይነት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ደግማችሁ ገልጻችኋል፡፡ እኛ ካላዘዝናችሁ የሚያዛችሁ ማነው? …” በማለት መልዕክት አስተላልፈውላቸዋል፡፡
እንደለመዱት አጭበርብረው ማለፍ የተሳናቸው የማኅበሩ አባላትም በቅርቡ (ማኅበሩንና አጋሮቹን) አስመልክቶ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተላለፈውን መመሪያና ደብዳቤ እንደሚቀበሉና መመሪያውም ትክክል እንደሆነና እንደሚደግፉት በጨው በታጠበ ዓይናቸው አረጋግጠው ተሸኝተዋል፡፡
They(MK) tried to tell us the other way round! Now we got the truth.
ReplyDeletemanem Aysemacheum Bekentu Atedkemu !! Enatem Manenetachun Leyu !!!
ReplyDelete